የኤፍ ኤስ አር ባለቤትና ሾፌር ነኝ። ከዚህ በፊት ስልኬን እንዴት በተሻለ መልኩ ለስራዬ መጠቀም እንደምችል በፍጹም መረጃው የለኝም ነበር። የጎጀብ ዶት ኮምን ማስታወቅያ ከፌስቡክ ላይ አንድቀን ተመለከትኩና የበለጠ ለመረዳት በፌስቡክ አዋራዋቸው። በድህረ ገጻቸውና በስልክ ያገኘውት መረጃ ስለማረከኝ የጎጀብ የተሽከርካሪ ባለቤትና አሽከርካሪዎች የሚለው መተግበሪያ አፑን ከጎግል ፕለይ አውርጄ የሚመቸኝን ቋንቋ መርጬ ተመዘገብኩኝ።
በመተግበርያው ፊት ገጽ ወኪል ምረጥ የሚለውን ክሊክ በማድረግ እዚሁ አዲስ አበባ ቅርብ ያለውን በመምረጥ መኪናዩን ገምግሞ እንዲያጸድቅልኝ የመኪናዬን መረጃና የጭነትና የተሳፋሪ መረጃዎችን በቀላሉ በማስገባት መዘገብኩት ። መኪናዪን እንደመዘገብኩኝ የማስታወቅያ ስጦታ አበረከቱልኝ። የሰላሳ ጉዞ ማስታወቅያ በነጻ እንዳስተዋውቅ የሚጠቅም ስጦታ ነበር። ከሰላሳ ደቂቃ በኳላ የመንጃ ፍቃዴን እና ሌሎች የቀሩ መረጃዎችን ጠይቀወኝ መኪናዬን አጸደቁልኝ። በዃላም ጉዞ ማቀድና ማስተዋወቅ እንድችል ፈቀዱልኝ።
እኔም የሳምንት የጉዞ እቅዴን እንደዚህ ወድያው እሁድ ቅዳሜ ጠዋት ነበር ያቀድኩት ከአዲስ አበባ ጅማ ሰኞ ረፋድ አስራ አንድ ሰአት ለመውጣት አቀድኩኝ ።12 ሰአት ጉዞው እንደሚፈጅብኝ ሲስተሙ ነገረኝ። ማክሰኞ ወደ ቀትር 6 ሰአት ገደማ ጂማ እደርሳልው። አራግፌ ተገቢውን እንቅልፍ ተኝቼና እረፍት አድርጌ እረቡዕ ረፋድ 11 ሰአት ከጅማ አዲስ አበባ ብመለስ በዬ አሰብኩኝ። ሀሙስ እረፋድ ወይም ከሰአት ሲል አዲስ አበባ እደርሳለው። ሀሙስ ከሰአት ባርፍ፣ አርብ ጠዋት ባራግፍ ብዬ አሰብኩኝ። ቅዳሜንና አሁድ አርፌ ሰኞ ደግሞ ከአዲስ አበባ መቀሌ ለመውጣት የሳምንቴን 3 ጉዞዎች አቅድኩኝና ጉዞዎቼን በጎጀብ መተግበሪያ በመጠቀም መዘገብኩኝ (ለማንኛውም ስልካቹ ላይ አፕ መጫን ካልቻላቹ ወኪላቹ እቅዳቹን ተቀብሎ ይመዘግብላቹዋል) ። እኔ ግን አራሴ የጉዞ መነሻ ፣ መድረሻ፣ ዋጋውን በኪሎ ፣ የመጫኛ ቅርብ ቦታ፣ የመኪና የመጫን አቀሜን መረጃ አስገብቼ ጉዞዎቼን መዝግቤ ጨረስኩኝ።
አዲስ አበባ ሰፈሬ ሀያት አርባ ዘጠኝ ስለነበር የመጫኛ ቦታዬን ወደ ሀያት ነበር የጉዞው መረጃው ላይ ያስቀመጥኩት። ስለዚህ የተለመደው የተጨናነቁና በደላላ የተዋከቡ የመጫኛ ቦታዎች ድረስ መሄድ ሳያስፈልገኝ ፣ መንገድ ተዛጋግቶ ሰአት ረፈደብኝ ምናምን ብዬ ሳልጨናነቅ እና አላስፈላጊ የነዳጅ ወጪ ሳላወጣ ጭነቶቼን እዚሁ በቅርብ ያሉትን መርጬ እንድጭን ያግዘኛል። እንደዚህ በየቦታው እየተንቀሳቀሱ መጫን መቻላችን እቃም የሚጭኑት ደንበኞቼ በተጨናነቀችው አዲስ አበባ ከቦታ ቦታ ሳይንከራተቱ፣ ደላሎች ጋር ሳይንከራተቱ በቅርብ ካሉበት ስፍራ፤ በፈለጉት ጊዜና በተመቻቸው ሁኔታ እንዲጭኑ ያስችላል ማለት ነው።
የጉዞ መረጃዎቼን አስገብቼ አክል ስለው ወዲያውኑ ለተሳፋሪና ጭነት ጫኝ ደንበኞች የጉዞ መፈለጊያ ድረገጽ እና መተግበርያ አፒ ላይ ስልኬን በማሳይትና የጉዞውን ዋጋ፣ መነሻና መድረሻ ቦታ እንዲሁም የጭነት ዋጋ መተዋወቅና መታየት ይጀምራል። አሁን በሀገሪቱ ዳር እስከዳር በሁሉም ቦታና ጊዜ የጉዞ እና የስራ መረጃየ እየተዋወቀልኝ ነው ማለት ነው።
ከተንሽ ደቂቃዎች በዃላ አንድ ደንበኛ ከጅማ መቀሌ 60 ኩንታል ቦቆሎ እንዳላቸው ጠየቁኝ። ገና ጅማ መች ደረስኩኝ በዬ መቀበል ፈራው። ነገር ግን የጅማ ጉዞዬ እርገጠኛ ስለሆንኩኝ የጂማውን ቦቆሎ ጭነት ቀድሜ ተቀበልኩት ና ቦታ ያዝኩላቸው።እሱም ደውሎ ማክሰኞ ማታ እንደሚያመቻችልኝና ወደ መቀሌም እራሴው እንድጭን ተነጋገርን (ከጂማ አዲስ አበባም እንደዚሁም ክአዲስ አበባ የመቀሌውንም ጭነት አገኘው ማለት ነው)
2ኛ ከ 3 ደቂቃ በኋላ ከአዲስ አበባ ወደጂማ የሚጫን ሸቀጥ እንደምጭን ተጠየኩኝ። ወድያው ተቀበልኩ።
3ኛ ከ አስር ደቂቃ በዃላ ሌላ ዴሊቨሪ ድርጅት ወደጂማ የሚላክ መለእክት ጠየቀኝ። ወዲያው ተቀበልኩት። ቀጥሎም አንድ ሰአት ሳይሞላ ፈርኒቸር ድርጅት የሚጭን ጠየቀኝና ተቀበልኩት። ሁለት ሰአት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለሰኞ ረፋድ ከአዲስ ጂማ ጉዞዬ ጭነት ጨርሼ ጉዞ ለማድረግ መዘጋጀት ጀመርኩኝ። ጅማ ሳልደርስ የጅማ አዲስ አበባንና መቀሌን ጭነት ጭምር ጭነት ቀድሜ አግኝቼ ነበር እና ከጅማ አዲስ አበባ እና ከ አዲስ አበባ ጅማ ጭነት መፈለግ አላስፈለገኝም። ጎጀብ መተግበሪያ ከደንበኛ ጋር በቀጥታ ከማገናኘቱ በተጭማሪ ቀድሜ ጉዞዬን እንዳቅድና ጭነት እዳገኝ፣ በተመቸኝ ቦታ እንድጭንና ወጪና ጉልበት ሳላባክን አቀላጥፌ እንድሰራ በተክኖሎጂው እረድቶኛል።
አሁን ሰላም ጉዞ ለማድረግ መኪናዬን ቼክ እያስደረኩኝ ነው
መልካም ጉዞ!!